Desktop Schools Popup

Select a School

Amharic - Letter, Student User Agreement, and Optional Protection Plan (Elem)

 

ዳይናሚክ ትምህርት በ1:1 ተደራሽነት

በበልግ 2019 ከ 4ኛ እና 5ኛ ክፍሎች የሚገቡ ተማሪዎች ወላጆች/አሳዳጊዎች፣

በዚህ በልግ ልጅዎ በትምህርት ቤት ሆነ በቤት ውስጥ መማርን ለመደገፍ የዲስትሪክት-ይዞታ የሆነ iPad_ይሰጠዋል/ይሰጣታል። ዳይናሚክ ትምህርት በ1:1 ተደራሽነት በዲስትሪክት 196 ውስጥ በአንድ ግብረ ኃይል በትምህርትና ቴክኖሎጂ ራእይ እና ማእቀፍ በ2013ተቋቋመ። ከዓመታት በ1:1 ቤታ ክፍሎች የመምህራን አቅም ግንባታ በኋላ እና እና በኅዳር 2015 በሕዝበ ውስጥ የገንዘብ ድጋፍ ለማግኘት የመራጮች ይሁንታ በማግኘቱ፣ መማርን ለመደገፍ እና ለማበልጸግ አንድ የዲስትሪክት-ይዞታ የሆነ iPad_ከ4ኛ-12ኛ ክፍሎች ለእያንዳንዱ ተማሪ ይሰጣል። ከመዋዕለ ህጻናት እስከ 3ኛ (K-3_)_ክፍል ያሉ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ውስጥ የቴክኖሎጂ ተደራሽነትን ለመጨመር ደግሞ ሂደት ላይ ነን።

ልጅዎ በትምህርት ዓመቱ መጀመሪያ ወር ውስጥ iPad_ያገኛል/ታገኛለች። ወደ ቤት ከመወሰዱ በፊት ተደጋጋሚ ተግባሮች እና አካሄዶችን በመመስረት

በዲጂታል ማህረሰብ ሃሳብ ልውውጥ አማካኝነት ተማሪዎችን ለመምራት iPad በክፍል ውስጥ ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል። መምህሩ ተማሪዎቹ መቼ መሳሪያውን ወደ ቤት እንደሚያመጡ ይወስናል።

በፊት FeePay ውስጥ የሚከተሉትን ሁለቱ ንጥሎች ላይ እርምጃ መውሰድ ይኖርብዎታል፦ የ iPad ከመቀበልዎ ኦገስት ውስጥ

 • ወደ FeePay መለያዎ ይሂዱ አና 19-20 iPad ተጠቃሚ ስምምነት (ክፍል 4-12) ተቀበል ወይም 19-20 iPad ተጠቃሚ ስምምነት (ክፍል 4-12) አትቀበል ያግኙ ። በአነዚህ ንጥሎች ውስጥ ሁለት ተግባራትን ያጠናቅቃሉ።
 1. አማራጭ የከለላ እቅድን መቀበል ወይም አለመቀበል፦ የዲስትሪክቱ-ይዞታ የሆነውን iPad 1:1 ተደራሽነት ለመሳተፍ ምንም ወጪ የለውም። ይሁን እንጂ አስፈላጊ ከሆነ ለተበላሹ ፣ ለጠፉ ወይም ለተሰረቁ iPads ለጥገና ወጭ ወይም ምትክ ቤተሰቦች ተጠያቂ ናቸው። በእነዚህ ምክንያቶች የተነሳ አማራጭ የከለላ እቅድ ለቤተሰቦች እየተሰጠ ይገኛል። አማራጭ የከለላ እቅድ ዝርዝር በተመለከተ ተያይዟል። አማራጭ የከለላ እቅዱን መቀበል ወይም አለመቀበል መፈለግዎን መወሰን ይችላሉ። ከኦክቶበር 16, 2019 በኋላ ሂደቱን ያላጠናቀቀ ማንኛውም ቤተሰብ የከለላ ዕቅድን እንዳልተቀበለ ሆኖ ይመዘገባል።
 2. የተማሪ የተጠቃሚ ስምምነት፦ ተማሪዎች እና ቤተሰቦች የ iPad የተማሪ ተጠቃሚ ስምምነት (ናሙና ተያይዟል) ውስጥ ያለውን መመሪያዎች እና የሚጠበቁ ነገሮችን ማክበር አስፈላጊ ነው። የእርስዎን የዲስትሪክቱ-ይዞታ የሆነውን iPad በመውጫው ቀን ቤት መውሰድ እንዲችሉ እርስዎ እና ልጅዎ የተማሪ የተጠቃሚ ስምምንት መስማማት ያስፈልጋል።

FeePay ለመድረስ እገዛ የሚያስፈልግዎ ከሆነ የልጅዎን ት/ቤት ያነጋግሩ።

 • የቤተሰብ መምሪያዎች እና የሚጠበቅብዎትን ማዘጋጀት በቤት ውስጥ iPad በተመለከተ። የሚከተሉትን ጥያቄዎች በተመለከተ የሚጠበቅባችሁን ነገሮች ለመወሰን ከልጅዎ (ልጆችዎ) ጋር አብሮ መስራት። በአንድ ላይ የቤተሰብ ሚዲያ እቅድም ማዘጋጀት ደግሞ ሊፈልጉ  ይችላሉ  (www.healthychildren.org/mediauseplan)
 1. ቤት ውስጥ የት ላይ ነው iPad መጠቀም የሚቻለው?
 2. ለምን ነገሮች ነው iPad መጠቀም የሚቻለው?
 3. በእያንዳንዱ ቀን በቤት ውስጥ iPad ላይ ለምን ያህል ጊዜ መቆየት አለብህ/ሽ?
 4. ማታ ላይ መሳሪያው የት ነው ባትሪ መሞላት ያለበት?

 

(FeePay ተጠናቅቋል)

የኤሌክትሮኒክ መሳሪያ አማራጭ የከለላ እቅድ

በዲስትሪክቱ-የሚሰጥ iPad የመሰሉ በዲስትሪክት 196 የመማር ቴክኖሎጂ ፕሮግራም አካል ሆነው ለተማሪዎች የተሰራጩ የግልኤሌክትሮኒክ መሳሪያ ያልተጠበቀ ብልሽት ለመሸፈን ለአንድ መሳሪያ በአመት $20 የከለላ እቅድ ሊገዙ ይችላሉ። የከለላ እቅዱ እንደ አማራጭ የቀረበ እንጅ አንድ ተማሪ መሳሪያውን ለመቀበል የሚጠበቅበት አይደለም። (ነጻ/ ቅናሽ ምሳ በቁ ለሆኑ ቤተሰቦች የቅናሽ-ክፍያ አማራጭ ይገኛል)።

የትኛው ተሸፍኗል፦

የከለላ እቅዱን ካልገዙ

 • ያልተጠበቀ ብልሽት – ለመጀመሪያ ጊዜ ሁሉንም ውስጣዊ እና ውጫዊ ክፍሎች ላይ ሙሉ ሽፋን (ክፍሎች እና የጉልበት) የመከተሉትንም በማካተት ያክላል፦
 • መስታውት እና LCD ማያ (ከመስታውቱ በታች የሚገኝ ድርብ
 • የጆሮ ማዳመጫ መሰኪያ ገመድ
 • አዝራሮች
 • ባትሪ
 • ማይክራፎን
የመከላከያ ሽፋን

 

 • ማስታወሻ፦ ተጨማሪ ጊዜ ያልተጠበቀ ብልሽት በተመሳሳይ ሽፋን ለእያንዳንዱ $40 ያስወጣል። ለሶስተኛ ጊዜ ያልተጠበቀ ብልሽት ከገጠመ፣ ተማሪው መሳሪያውን ለተሰየመው ቅጥር ሰራተኛ በእያንዳንዱ ቀን መጨረሻ ማስረከብ ይኖርበታል።
 • ስርቆት – የፖሊስ ሪፖርት ማካተት ይኖርበታል፣ ሁሉም የዲስትሪክቱ ኤሌክትሮኒክ መሳሪያዎች የመሰረቅ እድልን ለመቀንስ ሲባል ያሉበት ቦታ ዱካ ማግኘት እና እንዳይሰሩ ማድረግ ይቻላል።

ያልተሸፈነው ምንድን ነው፦

 • ብልሽቱ ሆን ተብሎ ከተደረገ ወይም በተማሪው ፍቃድ ከሆነ
 • መሳሪያው ከጠፋ (ያለ ፖሊስ ሪፖርት)
 • የኃይል ገመድ/መመጠኛ (በአምራቹ ዋስትና የተሸፈን ካልሆነ በስተቅር) - የመተኪያ ወጭ ግምት፦
  • Apple የኃይል ገመድ = $19
  • Apple ኃይል መመጠኛ = $19

የከለላ እቅድ ካልገዙ

የተማሪው ቤተሰብ ለምትክ (ከጠፋ ወይም ከተሰረቀ) እና ጥገና ወጪ ኃላፊነት አለባቸው። የመተኪያ እና በብዛት የተለመዱ የጥገና ግምታዊ ወጪዎች እንደሚከተለው ናቸው፦

ምትኮች

 • iPad = $299
 • የመከላከያ ሽፋን = $50

ጥገናዎች

 • የተበላሸ ወይም የተሰበረ LCD = $135
 • የተበላሸ ወይም የተሰበረ መስታውት = $95

የከለላ እቅዱ በየትኛውም የትምህርት ዘመን ውስጥ በማንኛውም ጊዜ ሊገዛ ይችላል። ነገር ግን የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ ከተሰጠ በኋላ ከተገዛ፣ መሣሪያው በቅድሚያ ደህንነቱን በሠራተኞች መመርመር አለበት። የከለላ ዕቅድ ይገዛም አይገዛም ማንኛውም በዲስትሪክቱ-የተሰጠ መሳሪያ ብልሽት፣ ጥፋት ወይም ስርቆት ወዲያውኑ ለሰራተኞች አባል ሪፖርት መደረግ አለበት።


 

(FeePay ተጠናቅቋል)

iPad የተማሪ ተጠቃሚ ስምምነት

እንደ የዲስትሪክት 196 ዳይናሚክ ትምህርት ለ 1:1 ተደራሽነት አካል በቤት እና በትምሕርት ቤት ጥቅም ላይ ሊውል የሚችል የዲስትሪክቱ-ይዞታ የሆነ መሳሪያ (iPad) ይቀርብልሃል/ሻል። የዲስትሪክቱ-ይዞታ የሆነውን መሳሪያ ሙሉ በሙሉ ለመጠቀም፣ ተማሪዎች እና ወላጆች ከዚህ በታች እና በጀርባ ላይ የተገለጸውን መመሪያዎች እና የሚጠበቁ ነገሮች ማክበር ይጠበቅባቸዋል። የእርስዎን የዲስትሪክቱ-ይዞታ የሆነውን መሳሪያ በመውጫው ቀን መውሰድ እንዲችሉ በ FeePay በኩል በመስመር ላይ ከታች ያሉትን ውሎች መስማማት ያስፈልገዎታል።

እባክዎን ልብ ይበሉ በቤትዎ ውስጥ ገመድ አልባ በይነመረብ ወይም ኢንተርኔት አገልግሎት ከሌለ፣ ልጅዎ ይዘቶችን፣ የተማሪ ስራ እና መተግበሪያዎችን ለማግኘት iPadን ከመስመር ውጭ ሊጠቀምበት ይችላል። ስለ ሌሎች ገመድ አልባ የበይነመርብ ተደራሽነት አማራጮች፣ እንደ ሞባይል ሆት-ስፖትስ እና ዝቅተኛ ዋጋ ዋይ-ፋይ አማራጮች ተጨማሪ መረጃ በልጅዎ ት/ቤት ይገኛል።

የዲስትሪክቱ-ይዞታ የሆነ መሣሪያ (iPad) ተረካቢ ተማሪ እንደመሆኔ መጠን…

መሳሪውን ለመማሪ እጠቀማለ መረጃዎችን በማግኘት እና በመተንተን፣ እና የሃሳብ ልውውጥ በማድረግ፣ ችግሮችን በመፍታት፣ እና አዲስ ነገርን በማፍለቅ እና በመፍጠር ትምሕርቴን አጠናክራለሁ።

መሳሪያውን ለመማሪያ ለመጠቀም እኔ…

 • የእኔን መሳሪያ የሃይል ማከማቻ ባትሪ ሙሉ በማድረግ በየዕለቱ ወደ ትምሕርት ቤት ይዤ እመጣለሁ፤
 • በሌላ ሰው የተዘጋጀን መረጃ ለንባብ ከማብቃቴ (ከመለጠፌ)፣ ከማሰራጨቴ ወይም ከመጠቀሜ በፊት ፈቃድ እጠይቃለሁ እና/ወይም ለባለመረጃው እውቅና እሰጣለሁ፤
 • ከሌሎች ጋር የሚኖረኝ ግንኙነት ኃላፊነት፣ አክብሮት እና ትህትና የተሞላበት ይሆናል፤
 • በመምሕር የተገለጹትን መተግበሪያዎች ብቻ አወርዳለህ፣ እና
 • በትምሕርት ክፍለ ጊዜ መሣሪያውን በአግባቡ እጠቀማለሁ።

 

ለመሳሪያው ጥንቃቄ አደርጋለሁ እና ስረከበው በነበርበት ሁኔታ መመለሱን አረጋግጣለሁ።

መሳሪያውን በመልካም ሁኔታ እንዲጠበቅ ለማገዝ እኔ…

 • ሁልጊዜም መሳሪያውን ዲስትሪክቱ በሰጠኝ መያዣ እይዛለሁ፤
 • መሳሪያውን፣ መያዣውን እና የኤሌክትሪክ ገመዱን ቀደም ሲል በተረከብኩበት በሚሰራ ይዞታው ለመመለስ ተስማምቻለሁሁ፤
 • መሳሪያው ቢጠፋ፣ ቢሰረቅ፣ ከተበላሸ ወይም በአግባቡ አልሰራ ካለ ወዲያውኑ ለመምሕሬ እና/ወይም ለተንቀሳቃሽ መሳሪያ ድጋፍ ልዩ ባለሙያ አሳውቃለሁ፤
 • መሳሪያው ከተሰረቀ ማናቸውንም አስፈላጊ የፖሊስ ሪፖርት በማቅረብ እተባበራልሁ።
 • መሳሪያው ለእኔ ተመድቦ ባለበት ጊዜ ለሚደርስ ማናቸውም ጥፋት ወይም ብልሽት የጥገና ወይም መተኪያ ወጪን ለመሸፈን ኃላፊነቱ የእኔ ሊሆን እንደሚችል ተስማምቻለሁ፤
 • በዲስትሪክት 196 የ iPad እንክብካቤ የመረጃ ምንጭ ገጽ ላይ የሚጠበቅብኝ አንብቤ እከተላለሁ፤
 • ለዚህ መሳሪያ ብቸኛ ተጠቃሚ እሆናለሁ፤
 • በእያንዳንዱ ምሽት ቤት ውስጥ መሳሪያውን በመሰካት ባትሪውን ሙሉ አደርጋለሁ፤
 • ት/ቤት ስሄድ ሆነ ስመለስ በጀርባ ቦርሳ ወይም የት/ቤት ቦርሳ እይዘዋለሁ፤
 • ከምግብ፣ ከፈሳሽ፣ ከማግኔት እና ከከፍተኛ ሙቀት ወይም ቅዝቃዜ አርቀዋለሁ፤
 • iPad ሲቆሽሽ በደረቅ ጨርቅ እወለውላሁ፣ እና
 • iPad ከእኔ ዘንድ በማይሆንበት ጊዜ አስተማማኝ እና ጥብቅ ቦታ አስቀምጣለሁ።

 

ኃላፊነት የተሞላበት ምርጫዎች አደርጋለሁ መሳሪያውን በመስመር ላይ እና ከመስመመር ውጭ ስጠቀም።

መሳሪያውን ስጠቀም ጥሩ ምርጫዎችን ለማድረግ እኔ…

 • ራሴን እና ሌሎች በበይነመርብ መስመር ላይ በመጠቀም ላይ ያሉትን ተቀባይነት ያለው የመረጃ ቴክኖሎጅ አጠቃቀም  ለተማሪዎች እና የተማሪ በይነመርብ መዳረሻ እና የመጠቀም ፈቃድ እስማማለሁ፤
 • በበይነመርብ አማካኝነት በእኔ ወይም በሌላ ሰው ላይ ከሥነ-ምግባር ውጪ የሆነ ተግባር መፈጸሙን ካየሁ ለአዋቂ ሰው አሳውቃለሁ፤
 • ለእኔ በተመደበ የአውታረ መርብ መለያ እጠቀማለሁ፤ ከእኔ መለያ ጋር ተያያዥ ለሆነ ተግባራት ሁሉ ኃላፊነት እወስዳለሁ፤
 • ካሜራ እና ቪድዮ የምጠቀመው በዲስትሪክቱ ፕሮግራም እንደ ተፈቀደው ከትምሕርት ጋር ተያያዥ ለሆነ አላማ ብቻ ነው፤
 • በማልጠቀምበት ጊዜ በይለፍኮድ እቆልፈዋልሁ፤
 • የእኔን የይለፍኮድ እና የይለፍቃል ለወላጆቼ እና ለትምሕርት ቤቱ ሠራተኞች ብቻ አጋራለሁ፤
 • በበይነመርብ ላይ የእኔን እና የሌሎችን ሰዎች የግል መረጃዎች እጠብቃለሁ፤
 • መሳሪያውን የምጠቀምበት እና ሌሎች ተግባራትን ማከናውንበትን ጊዜ አመጣጥናለሁ፤
 • በበይነመረብ መስመር ላይ የምለጥፈው ቋሚ እና የእኔ ዲጂታል አሻራ አካል መሆኑን ሁሌም ከግንዛቤ አስገባለሁ፤
 • ያለምንም ቅድመ ማሳወቂያ ወላጄ(ጆቼ)/አሳዳጊዬ(ዎቼ) እና የትምሕርት ቤቱ ሠራተኞች መሳሪያውን እንዲፈትሹ እና የእኔን አጠቃቀም እንዲከታተሉ በማንኛውም ጊዜ እፈቅዳለሁ፤ እና
 • ወላጄ(ጆቼ)/አሳዳጊዬ(ዎቼ) እና የትምሕርት ቤቱ ሠራተኞች መሳሪያውን እንዴት እና መቼ እንደምጠቀም በሚጠይቁኝ ጊዜ ለጥያቄዎቻቸው ሁሉ ምላሽ እሰጣለሁ።

 

ለ ተማሪ: ከዚህ በታች በመፈረም የዚህን ተጠቃሚ ስምምነት መጣስ የዲሲፒሊን እርምጃ እና በትምህርት ቤት ሥርዓቶች እና በዲስትሪክቱ 196 ፖሊሲዎች እና / ወይም በመሳሪያው የመጠቀም መብት እና ልዩ መብቶች መቋረጥ ሊያስከትል እንደሚችል ተረድቻለሁ።

____FeePay በኤሌክትሮኒክ ውስጥ ተከናውኗል___

የተማሪው ስም በእጅ ጹሁፍ

____FeePay በኤሌክትሮኒክ ውስጥ ተከናውኗል___

የተማሪው ፊርማ

______________

ቀን

 

ለ ወላጅ(ጆች)/አሳዳጊ(ዎች): በመፈረም፣ ከልጄ ጋር የ iPad የተማሪ ተጠቃሚ ስምምነትን እንደ አጤንኩት እና የቤተሰብ መገልገያ መሳሪያ ቪዲዮ መመልከታችንን እውቅና እሰጣለሁ። መሣሪያው ለልጄ በሚሰጥበት ጊዜ ለሚከሰቱ ማንኛውም መጥፋት ወይም ብልሽት ለጥገናዎች የሚደረግ ወጪ ወይም ምትክ ተጠያቂ እንድሆንኩ ተስማምቻለሁ።

____FeePay በኤሌክትሮኒክ ውስጥ ተከናውኗል___

የወላጅ/አሳዳጊ ስም በእጅ ጹሁፍ

____FeePay በኤሌክትሮኒክ ውስጥ ተከናውኗል___

የወላጅ/አሳዳጊ ፊርማ

______________

ቀን